አዲስ አበበ ህዳር 8/2015 (ኢዜአ) 5ኛው አዲስ ቻምበር ዓለም አቀፍ የማኑፋክቸሪንግና የቴክኖሎጂ ንግድ ትርዒት ዛሬ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ተከፍቷል፡፡ በመክፈቻ መርሃ ግብሩ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት መሰንበት ሸንቁጤን ጨምሮ ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። ዓለም አቀፍ የንግድ ትርኢቱ የገበያ ትስስር የሚፈጠርበት እና በዘርፉ የቴክኖሎጂ ሽግግር የሚከናወንበት መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል በመክፈቻ ስነስርዓቱ ላይ ተናግረዋል፡፡ መንግስት በሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያው ልዩ ትኩረት ከሰጣቸው ዘርፎች አንዱ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ነው ብለዋል፡፡ ዛሬ የተከፈተው ዓለም አቀፍ የንግድ ትርኢትም ለኢትዮጵያ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የገበያ ትስስር እና የቴክኖሎጂ ሽግግር በመፍጠር ረገድ ሚናው የላቀ ነው ብለዋል። የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት መሰንበት ሸንቁጤ በበኩላቸው፤ የንግድ ትርኢቱ በማኑፋክቸሪንግ ለተሰማሩ አምራቾች የገበያ ትስስር ለመፍጠር እንደሚያግዝ ጠቅሰዋል፡፡ አያይዘውም እንደነዚህ አይነት የንግድ ትርኢቶች መዘጋጀታቸው የሀገር ገፅታን ለመገንባትና ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት ትልቅ ፋይዳ አላቸው ነው ያሉት፡፡ በዓለም አቀፍ የንግድ ትርኢቱ ላይ ከ100 በላይ የሀገር ውስጥና የውጪ አምራች ኩባንያዎች፣ የቴክኖሎጂ አቅራቢዎች፣ አምራቾችና አስመጪዎች እንዲሁም ሌሎች ተቋማት ተሳትፊ ሆነዋል፡፡ ዓለም አቀፉ የንግድ ትርኢት ለአምስት ተከታታይ ቀናት ለጎብኚዎች በነፃ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ተገልጿል፡፡
Related Posts
Addis Chamber set to host International Manufacturing and Technology Trade Fair, next month
Addis Chamber has announced that the 5th edition of its International Manufacturing and Trade Fair under the Motto “Manufacturing for…
Addis Chamber concludes its 25th edition of Addis Chamber International Trade Fair.
A symposium entitled the nexus between “Ethiopia Tamirt” movement and the Export sector is held at the interluxury Hotel. Asfaw…
Addis Chamber Marks End of Year Thanks Giving Day Colorfully
Addis Chamber, one of the most influential BMOs marks its End of Year thanks giving date colorfully at the Sky…