አዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት የመስቀል አደባባይ እና አዲሱን የመኪና ማቆሚያ ሊያስተዳደር ነው

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የመስቀል አደባባይ እና የፓርኪንግ መሰረተ ልማቱን ለማስተዳደር ከከተማ  አስተዳደሩ ጋር ውል ተፈራርሟል፡፡
ንግድ ምክር ቤቱ የኢግዚቢሸን ማእከልና የገበያ ልማት ድርጅትን በመንግስትና በግል ዘርፍ ትብብር ማእቀፍ አማካኝነት ከ 1998 ጀምሮ እያስተዳዳረው የሚገኝ ሲሆን አደባባዩን፣ የመኪና ማቆሚያዎቹን እንዲሁም ሱቆቹንና መሰል አገልግሎቶችን እንዲያስተዳደር ተወስኖ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተጠናቀቁ ነው፡፡ ለዚህም ሲባል የምክር ቤቱ የዳይሬክተሮች ቦርድ ስራውን ለማስፈጸም የሚያስችል አዲስ መዋቅራዊ አደረጃጀት አጽድቋል፡፡
የኢግዚቢሸን ማእከሉ በሚሰጠው አገልግሎት ከመስቀል አደባባይ ጋር ግልጋሎታዊ ምግግብና ትስስር እንዲኖራቸው ይደረጋል፡።
የመስቀልአደባባይ ፕሮጀክት ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል እንዲፈጥር እተሰራ ነው፡፡ 1450 መኪኖችን የሚያስተናግደው የመኪና ማቆሚያ በአካባቢው እየታየ ካለው የንግድ እንቅስቃሴ እና የኩነት ብዛት ሳቢያ ለሚፈጠረውን የፓርኪንግ ችግር መፍትሄ ይሆናል ።
ንግድ ምክር ቤቱ እንደዚህ አይነቱን የኩነት ማስተናገጃ ቦታ የማስተዳደር ልምዱን ተጠቅሞ አደባባዩ ደረጃውን እና ዘመናዊነቱን ጠብቆ እንዲቆይ ለማድረግ ተዘጋጅቷል ፡፡ አዲሱ የመስቀል አደባባይ 35 ሱቆች እንዳሉት ይታወቃል፡።
ንግድ ምክር ቤቱ አደባባዩን እና የመኪና ማቆሚያውን ማስተዳደሩ የከተማ አስተዳደሩ እና አዲስ ቻምበር ያላቸውን አጋርነት የሚያጠናክር እና በሀገሪቱ እና በከተማዋ ያለውን ውጤታማ የግሉና የመንግስት አጋርነት አካሄድ የሚያሳይ ይሆናል ።
በቅርቡም ምክር ቤቱ ከከተማዋ የኢንቨስትመንት ቢሮና ከገቢዎች ባለስልጣን ጋር በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የጋራ መግባቢያ ሰነድ መፈረሙ የሚታወስ ነው፡።
አዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማእከልን ማስተዳደር ከጀመረ ወዲህ የማእከሉን ገቢ በጥቂት አመታት ውስጥ ከነበረው አመታዊ የተጣራ ትርፍ 1.8 ሚሊዮን ብር ወደ 32 ሚሊየን ማሳደጉን ከመረጃዎች ለማወቅ ተችሏል ።
አዲሱ የመስቀል አደባባይና የመኪና ማቆሚያ እንደ ሱቅ፤ የመጸዳጃ አገልግሎት፤የዲጂታል ስክሪን ፤ ውብ የሆኑ መናፈሻዎችን እና ሌሎች ጠቃሚ አገልግሎትን የሚሰጥ ስፍራ ሲሆን በከተማውም ሆነ በመላ ሀገሪቱ በአይነቱ የመጀመርያው ያደርገዋል፡፡
ምክር ቤቱ አደባባዩን በአዲሱ በጀት አመት መጀመሪያ/ ሀምሌ 1/ ማስተዳደር የሚጀምር ሲሆን ይህንን የከተማዋ እምብርት የሆነ ስፍራ 24 ሰአት ሳቢና የንግድና ኢንቨስትመንት መነቃቃት የሚታይባት ከተማ ልዩ ማሳያ ስፍራ ለማድረግ እቅድ ተይዟል፡።
ከዚህምበተጨማሪሲኤምሲአካባቢየሚገነባውበአዲስአፍሪካኢንተርናሽናልኤግዚቢሽንማዕከልናበኮንቬንሽንማዕከልግንባታየከተማአስተዳደሩናንግድምክርቤቱበጋራየሚሠሩሲሆን፣የአክሲዮንኩባንያተቋቁሞየከተማውአስተዳደርከ50 በመቶበላይየአክሲዮንድርሻእንዳለውይታወቃል፡፡
ይህየኮንቬንሽንማዕከልበአዲስአበባንግድናዘርፍማኅበራትጠንሳሽነትበአክሲዮንኩባንያደረጃተቋቁሞበርካቶችንባለአክሲዮኖችያደረገሲሆን፣አስተዳደሩግንከፍተኛውንየአክሲዮንድርሻይዟል፡፡

Our Sponsors

User login

 

Contact us

Addis Ababa Chamber of Commerce and Sectoral Associations, Trade and Investment Promotion Department

+ 251115 504647/48 OR +251911 212179

Fax: +251 11 550 4649