22ኛው አዲስ ቻምበር ዓለም ዓቀፍ የንግድ ትርኢት በአዲስ አበባ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) 22ኛው አዲስ ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርኢት በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው።
የአዲስ አበባ የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት፥ በቀጣዩ ወር በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የንግድ ትርኢት ላይ ለመካፈል ከ10 ሀገራት በላይ መመዝገባቸው ተገልጿል። 
በምክር ቤቱ የውጭ ግንኙነት እና ሚዲያ መምሪያ ሃላፊ አቶ ካሳሁን ማሞ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ በዚህ የንግድ ትርኢት ላይ ከጣሊያን ከ50 በላይ እና ከኬንያ ከ20 በላይ ኩባንያዎች ይሳተፋሉ።
“ንግድ ለልማት” በሚል መሪ ቃል የሚከናወነው የንግድ ትርኢቱ፥ በግብርና ማቀነባበያ፣ በአምራች ዘርፍ፣ በአገልግሎት እና ቴክኖሎጂ ውጤቶች ላይ ትኩረቱን በማድረግ የሚካሄድ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከ200 በላይ የሃገር ውስጥ እና አለም አቀፍ ኩባንያዎች ይሳተፋሉ።
የአዉሮፓ ህገራት ኩባንያዎች የንግድ ትርኢቱ ላይ ለመሳተፍ ያላቸዉ ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣጡንም ነዉ ሃላፊው የገለፁት።
የንግድ ትርኢቱ የልምድ ልውውጥ እና የንግድ ለንግድ ግንኙነትን ከመፍጠር ባሻገርም፥ በተለይ አነስተኛ እና ጥቃቅን ልማት ላይ የተሰማሩ ኩባንያች በቀላሉ ሊያመርቷቸዉ የሚችሉ፣ በገበያዉም ተመጣጣኝ የሆኑ የቴክኖሎጂ ምርቶች የሚቀርቡበት ይሆናል ነው የተባለው።

Our Visitors since February 2016

Free track counters

Contact us

Addis Ababa Chamber of Commerce and Sectoral Associations, Trade and Investment Promotion Department

+ 251115 504647/48 OR +251911 212179

Fax: +251 11 550 4649

abrahamgid@yahoo.com

Corporate Site - This is a contributing Drupal Theme
Design by WeebPal.